ምንጩ ፈለቀ
Menchu Feleqe
ትራክ 6 · 6:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ፍቅሩ የማይለወጥ የሚራራ አሃሃ
ምሕረቱ የበዛ ጌታ
ፍቅሩ የማይለወጥ ምሕረቱ የበዛ አሃሃ
አዝማች · Chorus
እንደ ጌታ ኢየሱስ ቢፈለግም ጠፋ (፪x)
እንደ ጌታ ኢየሱስ ሃሌሉያ ቢፈለግም ጠፋ
ቢፈለግም ቢፈለግም ጠፋ
(እንደ ጌታ) እንደ ጌታ ቢፈለግም ጠፋ
(እንደ ኢየሱስ) እንደ ኢየሱስ ቢፈለግም ጠፋ
(እንደ ጌታ) እንደ ጌታ ቢፈለግም ጠፋ
እንዳንተ ጌታ ብርቱ
እንዳንተ ብርቱ ኃያል
እንዳንተ ኃያል ኢየሱስ
ቢፈለግም ጠፋ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጊዜ አይቶ አይለወጥም
ፍቅሩ ወረት የለበትም
ዘለዓለም እርሱ እርሱ ነው
ኢየሱስ አፍቃሪ ነው
ሲወድም ምክንያት የለው
እንዲሁ አንዲሁ ነው
ዓለምን ሁሉ ወዶ
አዳነን ተአምር ሰርቶ
እግዚአብሔር እርህሩህ አምላክ
እግዚአብሔር ፃድቅ ነህ አምላክ
እግዚአብሔር እርህሩህ አባት
እግዚአብሔር ፃድቅ ነህ አምላክ
በምክርህ ቢሆን የምትደነቅ
በአገዛዝህ ከሁሉ የምትልቅ
አንተ ብቻ ትልቅ
ፈልጌያለሁኝ አላገኘሁም
እንዳንተ የሚሆን ጌታ ከቶ አላየሁም
አዝማች · Chorus
ክበር ክበር ክበር እግዚአብሔር
ንገሥ ንገሥ ንገሥ ኢየሱስ
ክበር ክበር ክበር እግዚአብሔር
ንገሥ ንገሥ ንገሥ ኢየሱስ
ምህረትህ ብዙ ብዙ ነው ጌታ
ምህረትህ ብዙ ብዙ ነው ኢየሱስ
ይቅርታህ ብዙ ብዙ ነው ጌታ
ይቅርታህ ብዙ ብዙ ነው ኢየሱስ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታዬ እንደ አንተ ያለ የት ይገኛል አሃ
በምሕረት በቸርነት የተሞላ (፪x)
ምህረቱን አበዛልኝ ለእኔ
ጌታዬ ስለወደደኝ አዳነኝ (፪x)
እናገራለሁ ደግሞ አወራለሁ
ስለ ምሕረቱ ስለ ቸርነቱ
እናገራለሁ ደግሞ አወራለሁ
ስለ ርህራሄው ስለ ደግነቱ
አያልቅምና ከቁጥር በዝቶብኛል
እንዲሁ ብቻ እዘምራለሁ
እንደ እግዚአብሔር የለም እላለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ውበትህ ልዩ ነው ፍቅርህም ግሩም ነው
አሰራርህ አሰራርህ አሰራርህ የሚወደድ ነው
ቀና ብዬ ወደ ሠማይ ዞር ብዬ ዙሪያዬን ሳይ
ጌታዬ ሆይ አጣሁልህ መሳይ (፪x)
ጌታዬ ልዩ ነው ልዩ ነው
ለእኔ ሃሌሉያ ለእኔ ሃሌሉያ በዘመኔ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ጨለማዬ በራ ብርሃን ወጣልኝ
በልቤ አየሁት ጌታዬን አወቅሁት
ምን ዓይነት አምላክ ነው እኔ የማመልከው
በጨለማ ይብራ ብርሃንን ያለው
አለቆች የቆፈሩት አዛውንቶች የማሱት
ነቢያት ብዙ ያሉለት ምንጩ ፈለቀ (፮x)
ምንጩ ፈለቀ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ