አንተ ትልቅ ነህ
Ante Teleq Neh
ትራክ 5 · 6:49 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንዴ አንጎዳጉደህ ሰማይን አናውጠሃል
ድንቀኛ አንጎዳጉደህ ምድርን አናውጠሃል
በኃይል አንጎዳጉደህ ሁሉን አናውጠሃል
አቤቱ እግዚኣብሔር አንተን ማን ይመስላል
በድምፅ ድንቀኛ ታንጎዳጉዳለህ
በኃይልህም ብዛት ሁሉን ታደርጋለህ
ግርማህ የሚያስፈራ ነው የሚያስደነግጥ
አዝማች · Chorus
አሠራርህ ግሩም እጅግ የሚወደድ (፪x)
ሥራህ ሥራህ ሥራህ ትልቅ ነው
ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የምድርን ዳርቻ በቃልህ ፈጥረሃል
ለወገግታም ደግሞ ሥፍራን አስታውቀሃል
ለብርሃን ሁሉ መኖሪያ አዘጋጅተህ
ከጨለማም ደግሞ ፈጽሞ ለይተህ
ሁሉን በጥበብህ በማስተዋል ሠራህ (፬x)
አቤቱ አምላኬ ሥራህ ግሩምና ድንቅ ነዉ (፬x)
አዝማች · Chorus
ሰማያት የአንተን ክብር ይናገራሉ
የሰማይ ጠፈር የእጅህን ሥራ ያወራል
እንዳንተ ከቶ ከቶ የት አል?
እኔም አላውቅህም አንተ ትልቅ ነህ (፮x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በሰማየ ሰማይ ሰማያቶች በምድርም ያሉ ፍጥረቶች
አዕዋፍ ሲዘምሩ ክብርህን ሲያወሩ ወንዞች በፏፏቴ አንተን ሲያናግሩ
አዝማች · Chorus
እኔ እገረማለሁ እገረማለሁ
እግዚኣብሔር ትልቅ ትልቅ ነው እላለሁ
እኔ እገረማለሁ እገረማለሁ
እግዚኣብሔር ትልቅ ትልቅ ነው እላለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ