Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አዋጅ ይነገር

Awaj Yeneger

ትራክ 10 · 4:23 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ውበቴን ንጉሥ ወዶ ማደሪያው አደረገኝ

በከበረው ስፍራ ላይ በቀኙ አስቀመጠኝ

እርሱ በሚኖርበት እኔ ደግሞ እንድኖር

ይኸው ተቀብሎኛል ጌታ እኔንም በክብር

አዋጅ ይነገር አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)

ንጉሥ ለወደደው እንዲህ ተደረገ

ንጉሥ ለሚወደው እንዲህ ተደረገ

እጅግ ባማረ ስፍራ ላይ እኖራለሁ በሠማይ (፪x)

አዋጅ ይነገር አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)

በዚህች በምድር ላይ በሥልጣን እንድኖር

በአሕዛብ ፈርጄ አለቆችን እንዳስር

ለእኔ ይህንን ክብር ጌታዬ አስረክቦኛል

ልጄ ወራሽ ነህ ብሎ ሁሉን በእጄ ሰጥቶኛል

አዋጅ ይነገር አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)

ንጉሥ ለወደደው እንዲህ ተደረገ

ንጉሥ ለሚወደው እንዲህ ተደረገ

በፍጥረታት ሁሉ ላይ ተሾምኩኝ ሆኜ የበላይ (፪x)

አዋጅ ይነገር አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)

ጠላት ባይገምትም እዚህ ይደርሳል ብሎ

የሃሳቤ ሳይሞላ እንድቀጠፍ በቶሎ

ግን በጌታዬ ልብ ውስጥ ስፍራ አገኘሁና

አብሬው ይኸው ቆምኩኝ ከእርሱ ጋራ ነገስኩና

አዋጅ ይነገር አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)

ንጉሥ ለወደደው እንዲህ ተደረገ

ንጉሥ ለሚወደው እንዲህ ተደረገ

በፍጥረታት ሁሉ ላይ ነገስኩኝ ሆኜ የበላይ (፪x)

አዋጅ ይነገር አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)

መቼ በምድር ብቻ አምሮብኝ የምኖረው

ገና ኢየሱሴ መጥቶ በክብር እነጠቃለሁ

ነዋሪ አይደለሁም አገር አለኝ በሠማይ

እኖራለሁኝ በዚያ ጭንቀት ስቃይን ሳላይ

አዋጅ ይነገር አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)

ንጉሥ ለወደደው እንዲህ ተደረገ

ንጉሥ ለሚወደው እንዲህ ተደረገ

እጅግ በተድላ ደስታ ይኸው አለሁ በጌታ (፪x)

አዋጅ ይነገር አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)

አዋጅ ፣ አዋጅ ፣ አዋጅ ፣ አዋጅ (፮x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ