እግዚኣብሔር ተዋጊ ነው
Egziabhier Tewagi New
ትራክ 1 · 5:19 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚኣብሔር ብርሃኔና መድሃኒቴ ነው (፬x)
የሚያስፈራኝ ከቶ ማነው (፰x)
እግዚኣብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው (፬x)
የሚያስደነግጠኝ ማነው (፰x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በረታለሁ ልቤን አጸናለሁ
እግዚአብሔርን ተስፋ አደርጋለሁ(፪x)
እግዚኣብሔር ተዋጊ ነው (፫x)
ሥሙም እግዚኣብሔር ነው (፪x)
ቁጣውን ሰደደ ጠላቶቼን በላ
በአፍንጫው እስትንፋስ ውሆችን ከመረ
ፈሳሾችም ደግሞ እንደ ክምር ቆሙ
ጠላቶቼን ሁሉ አሳድጄ ይዣለሁ
ምርኮን ተካፍዬ ነፍሴን አጥግቤያለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
አሃሃ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በክብር ከፍ ከፍ ጊዜ ብሏል (፪x)
ፈረስ ፈረሰኛውን ከባሕር ውስጥ ጥሏል
እግዚአብሔር ጉልበቴ ዝማሬዬ ሆኗል
ይሄ አምላኬ ነው እኔ አመልከዋለሁ
የአባቶቼ አምላክ ነው ከፍ አደርገዋለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
አሃሃ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አቤቱ ቀኚ በኃይል ከበረ (፪x)
አቤቱ ቀኚ በኃይል ከበረ (፪x)
ጠላትን ሁሉ መታ አደቀቀ
ጠላትን ሁሉ መታ አደቀቀ (፪x)
አቤቱ በአማልክት መካከል እንዳንተ ያለ ማነው (፬x)
በምሥጋና የተፈራ ድንቅን ነገር የምታደርግ
በቅድስና የከበረ እንዳንተ ያለ ማነው በዕርግጥ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ቀኝህን ዘረጋህ ምድር ዋጠቻቸው
ጠላቶች አለቁ ኃይልህ አቃታቸው
በቸርነት ብዛት ሕዝብህን መራኸው
ወደ ቅዱስ መቅደስ በኃይል አስገባኸው
አቤቱ እንዳንተ ያለ ማነው? (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ