Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እሰዋለሁ

Esewalehu

ትራክ 9 · 5:47 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በጉባኤ መካከል ስእለቴን እፈፅማለሁ

ሥራህንም እያየሁ እኔ እደነቃለሁ (፪x)

በሥራህ አንተ ፍፁም አምላክ ነህ

አትሳሳትም ሁሌ እውነት ነህ

አንተ ብቻህን ሁሉን ሰርተሃል

በሥራህ እኩያ ታጥቶልሃል (፪x)

ማስተዋልህ ጥበብህ

አይመረመር ዕውቀትህ

አስተዋይ ነህ ጌታዬ

እውነተኛ ነህ አምላኬ (፪x)

ሥራህ ግሩምና ድንቅ ነው

ሥራህ ግሩምና ድንቅ ነው

አቤቱ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ (፪x)

ሁልጊዜ ክብርህንና ግርማህን እዘምረዋለሁ

ለዘለዓለም ያረግኸውን ሁሉ ለትውልድ እናገራለሁ (፪x)

ሠማይና ምድርን ሞልተሃል

እግዚአብሔር ማን ይመስልሃል (፪x)

ማንንም አትፈራም ሁሉ ይፈሩሃል

እግዚአብሔር አንተን ማን ይቋቋምሃል (፪x)

ከማውቅህ በላይ ታላቅ ነህ

የእኔ ቃል አንተን አይገልፅህ (፪x)

እግዚአብሔር በከፍታ ድንቅ ነህ

የእኛ ጌታ በከፍታ ድንቅ ነህ

ድንቅ ነህ ፣ ድንቅ ነህ (፪x)

በመቅደስህ ድንቅ ነህ

በማደሪያህ ድንቅ ነህ

በዙፋንህ ላይ ድንቅ ነህ ፣ ድንቅ ነህ (፪x)

ይሄ ድንቅነትህ አስገርሞኛል (፪x)

ምሥጋና እንድሰዋ አስገድዶኛል (፪x)

እሰዋለሁ አልሰለችም እሰዋለሁ

እሰዋለሁ አልታክትም እሰዋለሁ

እሰዋለሁ ዛሬም ነገም እሰዋለሁ

እሰዋለሁ ለዘለዓለም እሰዋለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ