Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የእግዚኣብሔር ልጅ ኢየሱስ

YeEgziabhier Lej Eyesus

ትራክ 2 · 5:58 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የእግዚኣብሔር ልጅ ኢየሱስ በሰማያት በክብር ያለኸው

አምልኮና ስግደት ለአንተ ነው የሚገባው (፪x)

ክብሩ ከሰማያት በላይ ነው

እንደ አምላኬ እንደ እግዚኣብሔር

ኧረ ከቶ ማነው (፪x)

እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ(፬x)

በማን ትመሰላለህ

ከማንስ ጋር ትስተያያለህ (፪x)

ውሆችን በእፍኝህ የሠፈርክ

ሰማይን በሥንዝርህ የለካህ

እግዚኣብሔር አንተ እግዚኣብሔር ነህ

እግዚኣብሔር አንተ ግሩም ነህ

ከእልፍ የተመረጥክ ውበትህ ያማረ

ከምንም ከማንም እጅግ የከበረ

በሞገስ በግርማ በክብርም ያለህ

የአማልክት አምላክ ኢየሱስ አንተ ነህ (፪x)

በምሥጋና ልቀህ ታይ ጌታ (፬x)

ሃሌሉያ (፲x)

ኦ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ኦ ሃሌሉያ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ