አዲስ ምሥጋና
Addis Mesgana
ትራክ 7 · 4:54 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንተ ግን ያው አንተ ነህ (፬x)
ጊዜ አይለውጥህ ቦታ
ሥፍራ አይወስንህ ጌታ
ዕድሜ አይገድብህ ኢየሱስ
ዘመን አይሽርህ ንጉሥ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ኢየሱስ ኃያል ነህ
በጉልበትህ አቻ የሌለህ
ኢየሱስ ልዩ ነህ
በውበትህ መሳይ የሌለህ
አልፋ ኦሜጋ ዘለዓለማዊ
ያልህ የነበርክ ሁልጊዜ ኗሪ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኤልሻዳይ ፣ ኤልሻዳይ ከሁሉ በላይ
አዶናይ ፣ አዶናይ የሌለህ መሳይ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ምን ብዬ ላመስግንህ (፪x)
ስንቱን አውርቼ እዘልቀዋለሁ
ውለታህ ፣ ውለታህ ከአይምሮዬ በላይ ነው ጌታ (፪x)
አዝማች · Chorus
ለእግዚአብሔር አዲስ ምሥጋና (፫x)
ይብዛ ይብዛ ይብዛ እንደገና
ይብዛ ይብዛ ይብዛ እንደገና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ተዓምርን አድርጐና ማዳኑን አስታውቋልና
በአህዛብ ፊት ጽድቁን ገለጠ
ለያዕቆብ ምህረቱን ሰጠ
ለእስራኤል ቤት እውነቱን አሰበ
ለእኔም ደግሞ ምህረቱን አበዛ
ለእስራኤል ቤት እውነቱን አሰበ
ለእኔም ደግሞ ምህረቱን አበዛ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ