አልፋ ኦሜጋ
Alpha Omega
2018 · ትራክ 13 · 4:26 · አማርኛ
አቤቱ ለቀዳሚነትህ ጥንት
ለኋላኛናትህ ፍጻሜ የለህ [፪x]
አንተ እግዚአብሔር ነህ [፬X]
አልፋ ኦሜጋ ፊተኛ ኋለኛ [፬X]
ጌታ ዘመናትህ ዓማታትህ ቢቆጠሩ አያልቁም
ለአንተ ምን ቢበዙ የዕድሜ ገደብ ከቶ አይችሉም ሊሰጡህ
ዘመናትን አሳልፈህ አሳልፈህ
አንተ ብቻ ትኖራለህ ትኖራለህ
ዘላለማዊ ነህ
ዘላለማዊ ነህ [፬X]
አናልፍም ያሉ አለፉ
አንሞትም ያሉትም ሞቱ
ኃያላን ለአንተ ሰገዱ
ኃይል የእግዚአብሔር ነው አሉ
የአንተ አልፋ የአንተ ኦሜጋ
ሁሌ ጽኑ ነው መሽቶ ሲነጋ
መንግስትህ ቋሚ ዘላለማዊ
ሁሉ ሲያከትም አንተ ነህ ነዋሪ
ዘላለማዊ ነህ
ዘላለማዊ ነህ [፬X]
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ
አንተ ያልነበርክበት ጊዜ
ለቅጽበት አልነበረም አይኖርም
ስልጣንህ መንግስትህ ነው ከዘላለም [፬x]
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ