አንተ ታላቅ ነህ
Ante Talaq Neh
2018 · ትራክ 11 · 5:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር ሆይ እንዳንተ ያለ ማንም የለም (፪x)
አዝማች · Chorus
አንተ ታላቅ ነህ!
የስምህ ሥልጣን ታላቅ ነው! (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከጣዖታት ዘንድ ፊቴን አዙሬ
ለአንተ ክብር ሆነልኝ መዝሙሬ
ስል "አንተ እና ስምህ ታላቅ ነው!"
ሌላ ቃላት መግላጫ ባጣ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
አንተ ታላቅ ነህ
የስምህ ሥልጣን ታላቅ ነው (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ቢሰለፉ አማልክት በተርታ
ካንዳቸውም መሳይ የለ ጌታ
እንደ : ስምህ: ነህ የሁሉ ገዢ
ዘመንህ ዕድሜህ አይባልም ከዚህ
ልክ የለህም ወሰን የለህም
ልክ የለህም መጠን የለህም
በሰው ቋንቋ ከቶ አልገልጥህም (፪x)
ስምህ ትልቅ ነው ለጠራው ሁሉ 'ሚሆን መዳኛ
ስምህ ትልቅ ነው ለደካከመው ብርታት ማግኛ
አንተ ትልቅ ነህ በምንም ነገር ከቶ አትለካም
አንተ ትልቅ ነህ ዘመንህ አያልቅም የለብህ ድካም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ