ጌታ ልዩ ነው
Geta Leyu New
2018 · ትራክ 12 · 5:14 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ወደ ሕያው
አምላክ ተጠማች [፪X]
ቁጥር 1 · Verse 1
ልረካህ ብል እህህ
በቃኝ ልል ብል እህህ
አልችልም ኢየሱስ ሚጠገብ እኮ አይደለም
እሱ ልዩ ነው ልዩ [፪x]
ጌታ ልዩ ነው ልዩ [፪x]
ለታላቅነቱ ለታላቅነቱ
አዝማች · Chorus
ምስጋናውን አምጡ [፪x]
ቁጥር 2 · Verse 2
እፎይ እረካው የልቤ ደርሷል
አሁን ለጌታ ምለው ምን ቀርቷል
ብዬ ደምድሜ ገና ስል ቁጭ
ብሶ ይፈልቃል የዜማው ምንጭ
ብዬ ነበረ እንደዚህ ብዙ
ሚያቆም አይደለም የዜማው ወንዙ
ይሄን ስጨርስ ምለው ሌላ አለኝ
ጌታ ልዩ ነው የሚያዘምረኝ
አዝማች · Chorus
እሱ ልዩ ነው ልዩ [፪x]
ጌታ ልዩ ነው ልዩ [፪x]
ቁጥር 3 · Verse 3
ሌቤ የተመኘው ነገሬ ሳገኘው ደርሶ
የውስጥ ርካታና ደስታ አይሰጥ ጨርሶ
ሁሉንም ነገር አይቼ ስልችት ሲለኝ
ዛሬም ዘላለም ማይሰለች አንድ ጌታ አለኝ
ከዉሃ ይልቅ እኔ ሚጠማኝ
ከምግብ ይልቅ እኔ ሚርበኝ
የውስጤ ናፍቆት ኢየሱስ [፪X
የልቤ ናፍቆት ኢየሱስ] [፪x]
አዝማች · Chorus
እሱ ልዩ ነው ልዩ [፪x]
ጌታ ልዩ ነው ልዩ [፪x]
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ