ሙላኝ ተቆጣጠረኝ
Mulagn Teqotateregn
2018 · ትራክ 2 · 6:32 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጠልቄ መሄድ እፈልጋለሁ
የእኔ እርካታ የአንተ ክብር ነው
ላይ ላዩን መሄድ ይቅርብኝና
ይስጠም ሕይወቴ በህልውና (፪x)
መንፈስ ቅዱስ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሙላኝ ተቆጣጠረኝ
ሌላ ሕይወት አይኑረኝ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ላንብብ ቃልህን ልስማ ሕግህን
ላድርግ ስራዬን ደስ የሚልህን
መቅደስነቴ ለአንተ ብቻ ነው
የለኝም በአንተ ላይ ደባል የማደርገው
ከምር ነው ከልብ ነው
የአንተ መሆን ምፈልገው
ማንከስ ይቅር በሃሳቤ
ልከተልህ ቆርጦ ልቤ
አዝማች · Chorus
ሙላኝ ተቆጣጠረኝ
ሌላ ሕይወት አይኑረኝ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔ ግን እኔ ግን (፪x)
በጽድቅህ ፊትህን አያለሁ
ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ (፪x)
ቁርጭምጭሚት ጋ ባለው ሕይወቴ
በቃኝ አልበል በዚህ ረክቼ
ጉልበቴን እና ወገቤን አልፈህ
ተቆጣጠረኝ ከሁሉ ልቀህ
በአንተ ተይዞ ሁሉ ነገሬ
ቢያልቅ ይሻላል ቀሪ ዘመኔ
ጠልቄ መሄድ እፈልጋለሁ
የእኔ እርካታ የአንተ ክብር ነው
ላይ ላዩን መሄድ ይቅርብኝና
ይስጠም ሕይወቴ በህልውናህ (፪x)
መንፈስ ቅዱስ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሙላኝ ተቆጣጠረኝ
ሌላ ሕይወት አይኑረኝ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ