ድንቅ ነህ
Denq Neh
2018 · ትራክ 5 · 5:47 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌታ ፈጣሪዬ ስለ አፈጣጠሬ
ስለሚያስደንቀው ስለ አካል ክፍሌ
ላመሰግንህ እፈልጋለው
አዝማች · Chorus
ግሩም ድንቅ ሆኜ ተፈጥሪያለው [፪X]
ግሩም ነህ የሰራሀኝ
ድንቅ ነህ የፈጠርከኝ [፪X]
ቁጥር 2 · Verse 2
የማመስገኛ ምክንያት ከሆነ
ከቁጥር በላይ እኔ ጋር አለ
እግሬ ሲራመድ ሚዛን ጠብቆ
ዓይኔም ሲያይልኝ ቅርብም አርቆ
በራስ ቅሌ ላይ ሲበቅል ፀጉሬ
ጣቶቼ ላይ ሲያድግ ጥፍሬ
ውበት አላቸው በየቦታቸው
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታዬ አንተ ነህ የሰራሃቸው [፪X]
ግሩም ነህ የሰራሀኝ
ድንቅ ነህ የፈጠርከኝ [፪X]
ቁጥር 4 · Verse 4
ሰው ሰውን ቢሰራው
ቢያበጀው እስትንፋስ ቢሰጠው
የሚከፍለው አጥቶ
ሁሉም ሰው መኖር በተሳነው
ይተመን ቢባል በዋጋ የአካል ክፍሌ
በዓለም ያለው ሃብት በሙሉ አይመጥን ለኔ
እንዃን ሁሉንም ይቅርና አንዱንስ እንኳ
መፍጠር ያልቻለው የሰው ልጅ እንዴት ይመካ
ቁጥር 5 · Verse 5
ግሩም ነህ የሰራሀኝ
ድንቅ ነህ የፈጠርከኝ [፪X]
ቁጥር 6 · Verse 6
በሚጥም ዜማ የሚያዜመው የአንተን ዝማሬ
ገንዘብ ሊገዛው አይችል ይህ አንደበቴ [፪X]
ቁጥር 7 · Verse 7
ጌታ ፈጣሪዬ ስለ አፈጣጠሬ
ስለሚያስደንቀው ስለ አካል ክፍሌ
ላመሰግንህ እፈልጋለው
አዝማች · Chorus
ግሩም ድንቅ ሆኜ ተፈጥሪያለው [፪X]
ግሩም ነህ የሰራሀኝ
ድንቅ ነህ የፈጠርከኝ [፪X]
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ