Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ክብር ሁሉ

Keber Hulu

2018 · ትራክ 10 · 6:48 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንኳን ልመካ እንዲህ ነኝ ብዬ

እኔ እኔ ልል ቃል አስረዝሜ

'እ'ን አስጀምሮ 'ኔ'ን የሚያስጨርሰኝ

ከራሴ ምለው አንዳችም የለኝ

አሁን የሆንኩትን መሆን የመቻሌ

ጌታ በአንተ እኮነው አይደለም በእኔ

ክብር ሁሉ ለአንተይሁን x ፬

እኔ ለማለት "ፓ!" እንዲሉልኝ ሰዎች ብጠራ

ማንም አይገኝ በአሸዋ ላይ ቤቴን ስሠራ

እርሱ ነው ስል ግን ተሰብሰቡና "አዎ" በሉልኝ

ይህን ላረገው ታማኙ ጌታ (ክብር አምጡልኝ) x ፰

ስሙኝ ወገኖች ይህን ስናገር በሕይወቴ ላይ ለሆነው ነገር

እንኳን ልታበይ እኔን ላበዛ ትንፋሽ መንገዱን ከፍሎ እንደገዛ

ከቶ አልመካም እንዲያው በከንቱ ከእኔ ሳይሆን ሁሉ ነው በእርሱ

'እ' የሚለውን ፊደል ጀምሬ 'ኔ'ን ለመጨረስ ኃይል የለኝ እኔ

እያልኩኝ ነው በአንተ ነው ጌታ

ሁሉን አድርገህ የምታስመካኝ ሆንከኝ አለኝታ

ክብር ሁሉ ለአንተይሁን x ፬

ኧረ ምንድነው ከእኔ ነው የምለው

ኃይሌ ብርታቴ እጄ ያረገው

ማበዛላቸው ብዙ እኔዎች

ሆኑ ምላቸው በእኔ ክንዶች

ምንም የለኝም የሚያስብለኝ እኔ

ክብር ሚገባው ለአንተ ጌታዬ

እንኳን ልመካ እንዲህ ነኝ ብዬ

እኔ እኔ ልል ቃል አስረዝሜ

'እ'ን አስጀምሮ 'ኔ'ን ሚያስጨርሰኝ

ከራሴ ምለው አንዳችም የለም

ክብር ሁሉ ለአንተይሁን # ፬

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ