ነፍሴ ተስፋ
Nefse Tesfa
2018 · ትራክ 7 · 4:08 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ተስፋ እያደረገችህ
ምትዉልብህ ምታድርብህ
ህያዉ ተስፋዬ
ልቤ አንተን አምኖ ልቤ
ልቤ ባንተ ፀና ልቤ [፪X]
ቁጥር 1 · Verse 1
ጓዳዬን ሙላ አደባባዬን
ልኑር አንተን ስል ቀሪ ዘመኔን
ምንም አልሆንም አንተን ብያለሁ
የደህንነቴን እራስ ይዣለሁ
ልቤ ፀናልኝ አንተን በማመን
ፍጹም ነህ ጌታ የለብህ እንከን
ነፍሴ ትላለች ህያዉ ተስፋዬ
ከአዳኝ ወጥመድ መሸሸጊያዬ
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ተስፋ እያደረገችህ
ምትዉልብህ ምታድርብህ
ህያዉ ተስፋዬ
ልቤ አንተን አምኖ ልቤ
ልቤ ባንተ ፀና ልቤ [፪X]
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተን ያደረገ መድህን አንተን ያደረገ ጥላ
ሆነህለት አየሁ እንጂ ክፉ እንዳይነካዉ ከለላ
እኔስ ኧረ እኔስ ካሉት ከለላ ካሉት አጥር
[እንደምትበልጥ አይቻለዉ እግዚአብሔር] [፪X]
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ