ያው ነው
Yaw New
2018 · ትራክ 4 · 4:43 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዛሬ ብዬ የጠራሁት ቀን ትላንት ተብሎ አልፎ ሲወራ
ብርቱ መስሎ የታየው ሰው ለቀብሩ ሞቱ ሲሰማ
ፍጥረት ቦታውን ለቆ
የቆመው ደግሞ ወድቆ
ቀና ስል ኢየሱስ ያው ነው
ቀና ስል ጌታዬ ያው ነው ነው
አዝማች · Chorus
ይባላ ቀና ይባላ ቀና
ብርቱ የሆነ አምላክ አለና
ይታይ ወደ ላይ ይታይ ወደ ላይ
ዘላለም ሚኖር አለ በሰማይ
ቁጥር 2 · Verse 2
አለሁ አለሁ ያለው ሰው
ድንገት ጉልበት ሲከዳው
ሁሉን ዘመን በቃ ሲለው
እንደ ጥላ ሲያሳልፈው
ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ኢየሱስ ዛሬም ያው
ግርማዊነቱ ኢየሱስ ኢየሱስ ነገም ያው
አዝማች · Chorus
ይባላ ቀና ይባላ ቀና
ብርቱ የሆነ አምላክ አለና
ይታይ ወደ ላይ ይታይ ወደ ላይ
ዘላለም ሚኖር አለ በሰማይ
ቁጥር 3 · Verse 3
አደራ የተባለው ለአደራው ሳይበቃ
ዓይን የተጣለበት ከስፍራው ሲታጣ
ማነው ጽኑ ብዬ ስጠይቅ ጥያቄ
ቃሉ እንዲህ እያለ ፈሰሰ ከውስጤ
ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትናም ዛሬም እስከ ለዘላለም ያው ነው
አንቱ ተብሎ ሚወራለት
ጐንበስ ቀና ሚባልለት
እንዲያው ሲቀር በትዝታ
አንደ እለ ግን ሕያው ጌታ
ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ኢየሱስ ዛሬም ያው
ግርማዊነቱ ኢየሱስ ኢየሱስ ነገም ያው
አዝማች · Chorus
ይባላ ቀና ይባላ ቀና
ብርቱ የሆነ አምላክ አለና
ይታይ ወደ ላይ ይታይ ወደ ላይ
ዘላለም ሚኖር አለ በሰማይ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ