አልወጣም ከፊትህ
Alwetam Kefiteh
6:41 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ድምጹን እያሰማ ቀኔን የሚያበራ አላውቅም እንደጌታ
መጪውንም ዘመን ቀድሞ የሚናገር አላየሁም ከእርሱ በቀር
ለዘመኔ ባዳ እንዳልሆን እንግዳ ሚስጢሩን ይገልጸዋል በጓዳ
አምላኬ ኦ እንዴት እንዴት ልዩ ነህ (፪x)
አዝማች · Chorus
አልወጣም ከፊትህ (ከፊትህ) አይለየኝ መንፈስህ (መንፈስህ)
አላማዬ አንተ ነህ መኖሪያዬ
ሕይወት ትርጉም ያለው በአንተ ነው ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ድምጽህን ሰምቼ እረፍት ተሞልቼ ኖሬያለሁ ጸንቼ
ከአንተ ተጠግቼ ልብህን አግኝቼ ቀረሁኝ ገብቼ
ፊትህ እቆማለሁ ኃይልህን አያለሁ
አልወጣም ከክብርህ ውስጥ ወስኛለሁ
አምላኬ ሆ እንዴት እንዴት ልዩ ነህ (፪x)
አዝማች · Chorus
አልወጣም ከፊትህ (ከፊትህ) አይለየኝ መንፈስህ (መንፈስህ)
አላማዬ አንተ ነህ መኖሪያዬ
ሕይወት ትርጉም ያለው በአንተ ነው ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔስ አውቄያለሁ ሚስጥሩን አግኝቻለሁ
ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ
መነሻ መድረሻም አንተ ነህ ብያለሁ
ክብርህን ሳይ ጌታ እጠግባለሁ (፪x)
አምላኬ ሆ እንዴት እንዴት ልዩ ነህ (፪x)
አዝማች · Chorus
አልወጣም ከፊትህ (ከፊትህ) አይለየኝ መንፈስህ (መንፈስህ)
አላማዬ አንተ ነህ መኖሪያዬ
ሕይወት ትርጉም ያለው በአንተ ነው ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አልወጣም ከፊትህ
አልወጣም ከፊትህ (አልወጣም ከፊትህ) (፫x)
ከማደሪያህ ከመቅደስህ
አልወጣም ከፊትህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ