Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዙፋኑ ላይ

Zufanu Lay

6:11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዓይኖቼ አይተውህ እጅጉን ፈዘዙ

የፍቅርን እንባ አወጡ ከቶ ሳይታዘዙ

ነፍሴም አልቻለችም መድሃኒቷን ስታይ

ከጐኑ ስትሆን ከዚያ ዙፋኑ ላይ

ዙፋኑ ላይ ፤ ዙፋኑ ላይ ፤ ከዚያ ዙፋኑ ላይ (፪x)

በደሌ እንደሙታን አድንዞኝ ሳለሁ

በኢየሱሴ በኩል ወደአብ ዘንድ ገባሁ

በሥጋዬ ምኞት እየኖርኩኝ ሳለሁ

ከፍቅሩ የተነሳ ፀጋውን አገኘሁ

ዓይኖቼ አይተውህ እጅጉን ፈዘዙ

የፍቅርን እንባ አወጡ ከቶ ሳይታዘዙ

ነፍሴም አልቻለችም መድሃኒቷን ስታይ

ከጐኑ ስትሆን ከዚያ ዙፋኑ ላይ

ዙፋኑ ላይ ፤ ዙፋኑ ላይ ፤ ከዚያ ዙፋኑ ላይ (፪x)

ቸርነቱን ሊያሳይ ከእርሱ ጋር አስነሳኝ

በላይኛው ስፍራ በቀኙ አስቀመጠኝ

እንግዲህ አልመካም ከስራዬ አይደለም

በእምነት የተገኘ ስጦታ ነው ይኸው

ዓይኖቼ አይተውህ እጅጉን ፈዘዙ

የፍቅርን እንባ አወጡ ከቶ ሳይታዘዙ

ነፍሴም አልቻለችም መድሃኒቷን ስታይ

ከጐኑ ስትሆን ከዚያ ዙፋኑ ላይ

ዙፋኑ ላይ ፤ ዙፋኑ ላይ ፤ ከዚያ ዙፋኑ ላይ (፪x)

ጌታዬ ኢየሱስ አደንቅሃለሁ

በአንተ ውብ ፍቅር ተነድፌያለሁኝ (፪x)

ዓይኖቼ አይተውህ እጅጉን ፈዘዙ

የፍቅርን እንባ አወጡ ከቶ ሳይታዘዙ

ነፍሴም አልቻለችም መድሃኒቷን ስታይ

ከጐኑ ስትሆን ከዚያ ዙፋኑ ላይ

ዙፋኑ ላይ ፤ ዙፋኑ ላይ ፤ ከዚያ ዙፋኑ ላይ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ