Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጌታን ልባርከው

Gietan Lebarkew

4:38 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኑሮ ብዬ እኔ የያዝኩት

ሕይወት ብዬ የመረጥኩት

የሚተካ ያልተገኘለት

ኢየሱስ ነው የሰጠኝ እረፍት (፪x)

ከእርሱ ሌላም አልፈልግም

ሌላውም አልሞተልኝም

ያለኝን ሁሉ ብሰጠው

አይቆጨኝ ለእርሱ ባፈሰው

እስቲ ልባርከው ፣ እስቲ ልባርከው (፬x)

አለኝ ብዬ የምኮራበት

በታች አለው እኔን የሚያስንቅ

በብር በወርቅ የማይለወጥ

ኢየሱስ ነው ሰላም የሚሰጥ (፪x)

ልቤ ሚሻው የተጠማው

የማወጣው የማወርደው

መገኘቱ የሚናፍቀው

ሌላ አይደለም ኢየሱስ ነው

እስቲ ልባርከው ፣ እስቲ ልባርከው (፬x)

ከአምላኬ ጋር ውዬ ባድር

የሚመረር. (1) . አንዳች ነገር

ሌላ የለም ከእርሱ በቀር

ሕይወቴ ነው ጌታ እግዚአብሔር

ጌታ እግዚአብሔር (፪x)

ጌታን ልባርከው ጌታን ልባርከው (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ