Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጌታን ልባርከው

Getan Lebarkew

4:38 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኑሮ ብዬ እኔ የያዝኩት

ህይውት ብዬ የመረጥኩት

የሚተካ ያልተገኘለት

እየሱስ ነው የሰጠኝ እረፍት

፟

ከሱ ሌላም አልፈልግም

ሌላውም አልሞተልኝም

ያለኝን ሁሉ ብሰጠው አይቆጨኝ ለሱ ባፈሰው

እስቲ ልባርከው (..)

ሀይሌ ብዬ የምኮራበት

በታች ያለውን የሚያስንቅ

በብር በወርቅ የማይለወጥ

እየሱስ ነው ሰላም የሚሰጥ

ልብ የሚሻው የተጠማው

የማወጣው የማወርደው

መገኘቱ የሚናፈቀው/ሚፈለገው

ሌላ አይደለም እየሱስ ነው

እስቲ ልባርከው (..)

ከአምላኬ ጋር ውዬ ባድር የሚመረጥ

አንዳች ነገር ሌላ የለም ከሱ በቀር

ህይወቴ ነው ጌታ እግዚአብሄር

ጌታ እግዚአብሄር

ጌታን ልባርከው (..)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ