ሽልማቴ ነህ
Shilimateh Neh
5:10 · አማርኛ
ሁሉንም ትቼ እሮጣለሁ
ያለኝንም ሁሉ አጣዋለሁ
የሚጠቅመኝንም እተዋለሁ
ብቻ አንድ ነገር
አንድ ነገር እሻለሁ
እርሱንም አውቃለሁ
ሁሉም ቀርቶብኝ ቢገኝልኝ
የሱስ ነው ጉጉቴ የናፈቀኝ
በእርሱ ተገኝቼ እርሱንም አግኝቼ
ሌላ መሻት የለኝ የምራበው
የሱስ ዕንቁዬ ነው
እርሱን ከማወቅ ጋር ምን ይወዳደራል
ሁሉን እርግፍ አድርጐ አስትቶ ያስኬዳል
ሽልማቴ ሌላ መች ለእኔ ሆነልኝ
አዝማች · Chorus
እርሱ ነው ኢየሱስ እኔን የወደደኝ (፪x)
ሽልማቴ ነህ የእኔ ጌታ
ሽልማቴ ነህ የእኔ ኢየሱስ (፪x)
ሆነህ ተገኝተሃል በእኔ ዘንድ አንደኛ
ሁሉንም አስናቀኝ ኢየሱስ የእኔ እረኛ (፪x)
የከበረ የገነነ እኔ እምሻው ኢየሱስ ነው (፲፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ