በራሱ ምሎ
Berasu Melo
5:32 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጽዋ ሲሞላ ሰዓቱ ሲደርስ
የጌታ ሞገስ በእኛ ላይ ሲፈስ
ከፍታውም ዝቅ ሸለቆውም ከፍ
ካለ በኋላ ጌታ ይላል ከተፍ (፪x)
አዝማች · Chorus
በራሱ ምሎ በገዛ ክንዱ
ጣልቃ የሚገባ ኧረ ማነው እርሱ
እግዚአብሔር ነው እንጂ ቀን የሚቀጥረው
ያልተጠበቀን ነገር የሚያደርገው (፪x)
ገና ብዙ አለ በመዝገቡ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እርሱ ጌታዬ መሆኑን አይቼ
እጮሃለሁኝ እጆቼን አንስቼ
የማላቀውን ነገር የሚያሳየኝ
እንደእግዚአብሔር ኧረ የት ሊገኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
በራሱ ምሎ በገዛ ክንዱ
ጣልቃ የሚገባ ኧረ ማነው እርሱ
እግዚአብሔር ነው እንጂ ቀን የሚቀጥረው
ያልተጠበቀን ነገር የሚያደርገው (፪x)
ገና ብዙ አለ በመዝገቡ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ ጌታ ጌታ ነውና
ስለቤቱ የሚቀና
ቃል የገባውን ይፈጽማል
ተስፋውንስ መቼ ያጥፋል (፫x)
ገና ብዙ አለ በመዝገቡ (፪x)
ገና ብዙ አለ (ብዙ አለ)
ብዙ አለ (ብዙ አለ)
ብዙ አለ በመዝገቡ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ