Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መቼ ዝም ያሰኛል

Mechie Zem Yasegnal

4:27 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምሥጋና ይሞላ ሁልጊዜ አንደበቴ

ለጸሎት ይንበርከክ እስኪዝል ጉልበቴ

አፌም ይንቀሳቀስ ያውራ ስራህን

ምላሴም ይናገር ይበል ክብርህን (፪x)

መቼ ዝም ያሰኛል ብዙ ነው ውለታህ

ለእኔ ያደረከው ድንቅ ተዓምራትህ

ኦ ድንቅ ተዓምራትህ (፪x)

አጽናናህ አበረታህ ቁርጭምጪሚቴን

እየሮጥኩኝ ላውራ ሜዳ ዳገቱን

ይህ የመዳን ወንጌል ለዓለም ይዳረስ

በሠማያዊው ጠል ነፍስ ሁሉ ይረስርስ (፪x)

መቼ ዝም ያሰኛል ብዙ ነው ውለታህ

ለእኔ ያደረከው ድንቅ ተዓምራትህ

ኦ ድንቅ ተዓምራትህ (፪x)

ላላወቁህ ሁሉ ቀርበው ላልቀመሱ

መናገር እንድችል ሙላኝ በመንፈስህ

ሕይወቴ አርክቶህ ወዳንተ እስክደርስ

ምስክር አድርገህ ለክብርህ አቁመኝ (፪x)

መቼ ዝም ያሰኛል ብዙ ነው ውለታህ

ለእኔ ያደረከው ድንቅ ተዓምራትህ

ኦ ድንቅ ተዓምራትህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ