ክብር ያስመለሱ
Keber Yasmelesu
3:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክብር ያስመለሱ መሰውያን ያደሱ
ሁሉም የረሱትን በእድሜያቸው ያነሱ
እግዚአብሔርን ሽተው ታሪክ ያስለወጡ
በየዘመናቸው ለእውነት የተሰጡ
ነበሩ አምላካቸውን ፈገግ ያስደረጉ
አዝማች · Chorus
ከእጁ ይልቅ ፊቱን ለልብ/ከምር የፈለጉ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በዘመኔ ሁሉ እኔም ሌላ አልሻም
አንተን እንጂ ጌታ ሌላ አላሳድድም
በልቤም ዙፋን ላይ ሌላ አይቀመጥም
ለአንተ እንጂ አምላኬ ለማንም አይሆንም
ቁጥር 3 · Verse 3
ብዙዎች ረክተዋል የእጅህን ስራ አይተው
እንጀራም ተርበው ስላበላሃቸው
በከንቱ ፈለጉህ ደግመህ እንድጸጣቸው
በቃኝ በማያውቀው ከንቱ መሻታቸው
ቁጥር 4 · Verse 4
እኔ ግን አንዲት ነገር እለምንሃለሁ
አዝማች · Chorus
ከምትሰጠኝ በላይ አንተኑ እሻለሁ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ወደቀኝም ሳልል ወደግራም ሳላይ
የመደበልኝን ተቀብዬ ከላይ
ሩጫዬን እሮጣለሁ እርሱ እየመራኝ
በመጨረሻው ቀን በእጣ ክፍሌ እንድገኝ
ወሰንኩኝ ላልመለስ እስከመጨረሻ
አዝማች · Chorus
ከአምላኬ በስተቀር ልቤም ሌላ አይሻ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ