እኔም እፊትህ
Eniem Efiteh
5:25 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክብርህን ያዩ ወደው የተገዙ
ከመንፈስ ውኃ በ. (1) . የጠገ
ከዓለም ተለዩ አንተን ወደዱ
የሙጥኝ ብለው ግርማህን አዩ
አዝማች · Chorus
እኔም እፊትህ ዛሬ እወድቃለሁ
ክብርህን ሳላይ መቼ እነሳለሁ
ተጠማሁ ጌታ ሙሉ ግርማህን
ጆሮ ያልሰማውን ዓይንም ያላየውን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቃልህን በግልጥ እንዲናገሩ
ተሰበሰቡ አንተን ሊጠሩ
ክብርህም ወርዶ አንደበት ነካ
የመገለጥ ቃል አፋቸው ሞላ
አዝማች · Chorus
እኔም እፊትህ ዛሬ እወድቃለሁ
ክብርህን ሳላይ መቼ እነሳለሁ
ተጠማሁ ጌታ ሙሉ ግርማህን
ጆሮ ያልሰማውን ዓይንም ያላየውን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ያላስተዋልኩት ከቶ ያላየሁት
ድካሜ ይውጣ በሠማይ እሳት
ልትሰራ ጌታ ክብርህን እንዳይ
ይውረድ በእኔ ላይ ደመናህ ከላይ
አዝማች · Chorus
እኔም እፊትህ ዛሬ እወድቃለሁ
ክብርህን ሳላይ መቼ እነሳለሁ
ተጠማሁ ጌታ ሙሉ ግርማህን
ጆሮ ያልሰማውን ዓይንም ያላየውን (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ቀንና ሌሊት ፊትህ እወድቃለሁ
ክብርህን እንዳይ እዋረዳለሁ
ደግሞም ኢየሱስ እንደነበረ
ትሁት አገልጋይ የተሰበረ
አዝማች · Chorus
እኔም እፊትህ ዛሬ እወድቃለሁ
ክብርህን ሳላይ መቼ እነሳለሁ
ተጠማሁ ጌታ ሙሉ ግርማህን
ጆሮ ያልሰማውን ዓይንም ያላየውን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ