አመለጥን
Ameleten
ትራክ 6 · 4:43 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ድንቅ ነገር ነው ያደረገልን (፪x)
ሳንጠፋ ቀኑ ሳይጨልም ደረሰልን (፪x)
እግዚአብሔር ድንቅ ነገር ነው ያደረገልን (፪x)
ሳንጠፋ ሳይመሽብን ደረሰልን (፪x)
ወጥመዱ ተሰባበረ እኛም አመለጥን (፪x)
አመለጥን (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አይቶ ልቡ አልችል ሲለው አንድያ ልጁን ሰደደው (፪x)
አይቶ ልቡ አልችል ሲለው የኔ ጌታ አንድያ ልጁን ሰደደው (፪x)
ወዶ ስለመረጥኝ በአብ ቀኝ አስቀመጠኝ (፪x)
ወዶ ስለመረጥኝ ኢየሱሴ በአብ ቀኝ አስቀመጠኝ (፪x)
ተናጠቀልኝ ጠላቴን ተበቀለልኝ (፪x)
ተናጠቀልን ጠላትን ተበቀለልን (፪x)
አመለጥን (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የእግዚአብሔር ምሕረቱ ስፋቱ ጥልቀቱ (፪x)
የጌታዬ ቸርነቱ ብዛቱ ጥልቀቱ (፪x)
አይደረስበትም (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አንድያ ሆኖ ከሰማያት መጣ
በኩር ሆኖ ወደሰማይ ገባ
ወንድሞቹን አስከትሎ ኋላ
አንድያ ሆኖ ከአባቱ እቅፍ ወጣ
በኩር ሆኖ ወደአባቱ ገባ
እኛን እኛን አስከትሎ ኋላ
ቁጥር 4 · Verse 4
ጠላቴ ከንቱ ነው ልፋቱ ከንቱ ነው
እኔ እንደሁ በኢየሱስ ካመለጥሁ ቆየሁ
ጠላቴ ከንቱ ነው እሩጫው ከንቱ ነው
እኔ እንደሁ በኢየሱስ ካመለጥሁ ቆየሁ
እኔ እንደሁ በጌታ ካመለጥኩ ቆየሁ
እኔ እንደሁ በኢየሱስ ካመለጥሁ ቆየሁ
አመለጥቁኝ (፮x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ