አይበዛብህም
Aybezabehem
ትራክ 7 · 7:12 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ገንኖ ገንኖ ስምህ መውጣቱ
ፍጥረት ሁሉ ስላንተ ማውራቱ
ከፍታ ላይ አለመድረሱ ይሄ ሁሉ ማዕረጉ
አዝማች · Chorus
ልክ ነው አይበዛብህ እንዲያውም ስያንስብህ (፫x)
ማን ብሎህ ከበርህ አንተ እራስህ ክቡር
ማን ሾሞህ ነገስህ አንተ እራስህ ንግስ
ማን ብሎህ ክቡር ሆንክ ማን ሾሞህ ነገሥህ (፪x)
አንተ እራስህ ክቡር ነህ (፪x)
አንተ እራስህ ንጉስ ነህ (፪x)
እራስህ አንተ እራስህ ክቡር ነህ
እራስህ አንተ እራስህ ንጉሥ ነህ
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታዬ እኔ ከምልህ አንተ ያለህ ብዙ ነው
ስለገረመኝ ብቻ እንዲህ ነህ እልሃለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ምስጋናዬን እሰማለሁ በከንፈሬ
የወጣው ግን የሞላው ነው ነው ከልቤ
አምልኮዬን እሰማለሁ በከንፈሬ
የወጣው ግን የሞላው ነው ከልቤ
ከልቤ ነው ከልቤ አይደለም በከንፈሬ (፪x)
ዝማሬዬን አሰማለሁ በከንፈሬ
የወጣው ግን የሞላው ነው ከልቤ
አድናቆቴን አሰማለሁ በከንፈሬ
የወጣው ግን የሞላው ነው ከልቤ
ከልቤ ነው ከልቤ አይደለም በከንፈሬ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ክበር ይላሉ ንገሥ ይላሉ
በሰማይ ያሉ በምድር ያሉ
ሲሉህ ሰምቼ ልልህ ቆምኩኝ
እኔም የራሴ ምሥጋና አለኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
አለኝ ምሥጋና አለኝ
አለኝ ዝማሬ አለኝ
አለኝ አምልኮ አለኝ
አለኝ አድናቆት አለኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ