ክብር ለአንተ
Keber Lante
ትራክ 5 · 6:41 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጠዋት ሳልል ማታ አቀርባለሁ ምሥጋና (፪x)
ጠዋት ሳልል ማታ እሰዋለሁ ምሥጋና (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ዕለቱን ሙሉ ክበር ብዬ ብዬ አይበቃኝም
እንዲሁማ በቀላሉ አይወጣልኝም
ዕለቱን ሙሉ ንገሥ ብዬ ብዬ አይበቃኝም
እንዲሁማ በቀላሉ አይወጣልኝም
ክበር ብዬ ሳልጨርስ ይመሽብኛል ይመሽብኛል
ንገሥ ብዬ ሳልጨርስ ይነጋብኛል ይነጋብኛል (፪x)
ዕለቱን ሙሉ ክበር ብዬ ብዬ አይበቃኝም
እንዲሁማ በቀላሉ አይወጣልኝም
ዕለቱን ሙሉ ንገስ ብዬ ብዬ አይበቃኝም
እንዲሁማ በቀላሉ አይወጣልኝም
አዝማች · Chorus
ጌታ ተብሎ ምን ይቀጠላል (፪x)
የምጋሥና ቃል ሁሉም አንሶሃል (፪x)
አምላክ ተብሎ ምን ይቀጠላል (፪x)
የዝማሬ ቃል ሁሉም አንሶሃል (፪x)
አንተን ማምለኪያ (፪x)
እስከዛሬም አንሷል ቢጨመርም ያንሳል
እድሜ ልክም ያንልሳል ዘላለምም ያንሳል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ግን ያለኝን አልቆጥብም
ያንሳል ብዬ አላቆምም (፪x)
ዳር ዳር አልልም አንተን ለማመስገን
አገባለሁ ምስጋናው መሃል (፪x)
ዳር ዳር አልልም አንተን ለማመስገን
አገባለሁ አምልኮ መሃል እገባለሁ ዝማሬው መሃል
ማልችለው አለማምለክ ነው ምያቅተኝ አለማምለክ ነው
አምልኮ አውቅበታለሁ እንዲያውም አሳምራለሁ (፪x)
እኔ ምያቅተኝ እኔ የማልችለው
አለማመስገን አለማምለክ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ (፲፪x)
ክብር ለአንተ እንጂ ለማን ይሰጣል (፪x)
ክበር ለአንተ ነው እንጂ ለማን ይገባል (፪x)
ከትላንት ይልቅ ዛሬ አንተን ላከብር
ተነሳስቻለሁ ተነሳስቻለሁ (፪x)
ክብር ለአንተ እንጂ ለማን ይሰጣል (፪x)
ክበር ለአንተ ነው እንጂ ለማን ይገባል (፪x)
የአንተን ምሥጋና ለማንም አልሰዋም (፪x)
የአንተን ክብር ለማንም አልስጠም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ