አቤት አምላኬ
Abiet Amlakie
ትራክ 1 · 5:31 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቤት አምላኬ ያደገልኝን ሳስተውለው ባረኩህ (፪x)
የእኔ ጌታ ያደረክልኝ ሳስተውሰው ወደድኩህ (፪x)
ለካስ እንዲህ ነው (፫x)
ነፍሴን ያዳንካት ከጉድ ነው
ለካስ እንዲህ ነው (፫x)
ነፍሴን ያዳንካት ከሞት ነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የዘለዓለም ፍቅር የዘላለም ሕይወት
ይሄው አሰጥቶኛል ወደ አብ መግባት
ኢየሱስ አየሁት የፍቅርህን ልኩን
አኔ አስገዝቶኛል እስከ ሞት መሆኑ
ማንም ባያውቅህ የታወቅህ ነህ
ማንም ባያምንህ የታመንህ ነህ
እኔስ አውቄህ ሆንኩኝ ምስክር
ሳላመነታ ሳልደናገር (፪x)
እኔስ አውቄ ሆንኩኝ ምስክር
ሳላመነታ ሳልጠራጠር
ቁጥር 2 · Verse 2
ታሪክ ተረድቼ አይደለም ሲነገር ሰምቼ ብቻ አይደለም
የሰራህልኝን አስቤ እከተልሃለሁ ከልቤ
ታሪክ ተረድቼ አይደለም ሲነገር ሰምቼ ብቻ አይደለም
ያደረክልኝን አስቤ እኖርልሃለሁ ከልቤ
አውቄያለሁ አውቄያለሁ ተረድቻለሁ
የመኖሬ ትርጉም ሆኖ አግኝቼዋለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አቤቱ እንዳንተ ለኔ ማነው
ማንስ ነው ልሙትልሽ ያለው
ከሰማያት ወርደህ ያዳንከኝ አንተ
ለዘለዓለም ልገዛልህ ላንተ
ከሰማያት ወርደህ አድነህኛል
የሰራህልኝን ልቤ አውቆታል
ሳመልክህ በደስታ ሳከብርህ በደስታ
ለነፍሴ በሞት ፈንታ መዳን አውጀሃልና (፪x)
አዝማች · Chorus
እንግዲህ ነፍሴን ካዳንክልኝማ
በደስታ እኖራለሁ በደስታ ላንተ ጌታ
በደስታ እኖራለሁ በደስታ
እንግዲህ ነፍሴን ካዳንክልኝማ
በውዴታ እገዛለሁ በውዴታ ላንተ ጌታ
በውዴታ እገዛለሁ በውዴታ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ