Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምትክ የለህ

Metek Yeleh

ትራክ 10 · 3:40 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንደ እናት ነህ አልልም

እንደ አባት ነህ አልልም

ምትክ የለህ መድህኔ

አንድ እኮ ነህ ለእኔ (፪x)

አንድ ነህ ለእኔ ጌታ

የለኝም የማቆመው/የምተካው በአንተ ቦታ (፪x)

አንዱ ሲመጣ አንዱ ይሄዳል

በምድር ያለው ይቀያየራል

ኢየሱሴ ካንተ የተለየ ሰው

ባንተ ቦታ የሚቆምለት ማነው (፪x)

አንተ የእኔ ጌታ

አንተ ማን ሊተካ

አንተ የእኔ አምላክ

አንተ የለም ምትክ (፪x)

ለእኔስ አንተ ነህ መሪዬ

የቅርቡ ተጠሪዬ

የቅርቡ ተጠሪዬ (፪x)

ከአንተ ሌላ ለእኔ ማነዉ (፪x)

ከአንተስ ሌላ ለእኔስ ለምኔ (፪x)

ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ይጣፍጣል (፪x)

ፍቅርህ ከማር ወለላም ይመረጣል (፪x)

ይመረጣል አሃሃ ይመረጣል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ