ደጄን ዘግቼ
Dejien Zegechie
ትራክ 2 · 6:30 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ደጃፌን ዘግቼ ስልህ አንተ ትሰማኛለህ (፪x)
በስውር የነገርኩህን በግልጽ ትቀፍለኛለህ (፪x)
እገባለሁ በሬን እዘጋለሁ
ልቤን ደግሞ ላንተ አሳይሃለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሚረዳኝ የሚረዳኝ ነው (፪x)
ለኢየሱስ ነገሬን ለሚያውቀው
ልግባና የልቤን ላዋየው
ሚረዳኝ የሚረዳኝ ነው (፪x)
ለኢየሱስ ነገሬን ለሚያውቀው
የልቤን ነግሬው አልፋለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ወደ እልፍኜ ገብቼ
በሬን ደግሞ ዘግቼ
የልቤን ለአንተ ለአንተ አዋያለሁ
ለሰው ባወራው ምን አገኛለሁ
የልቤን ለአንተ ለአንተ አዋያለሁ
ለሰው ባወራው ምን አገኛለሁ (፪x)
እገባለሁ በሬን እዘጋለሁ
ልቤን ደግሞ ለአንተ አሳይሃለሁ (፪x)
ትካዜዬን በአንተ ላይ እጥላልሁ
የምትደግፍ አንተን ስላየሁ (፪x)
ለሰው አላወራም ትርፉ መባከን ነው
የልብ የሚረዳ ጌታ እንዳንተ ማነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ከአንተ በላይ ወዳጅ ማን አለ
ከአንተ በላይ ረዳት እኮ ማን አለ
ከአንተ በላይ ተስፋ ማን አለ
ከአንተ በላይ ረዳት እኮ ማን አለ
እግዚአብሔር እንዳንተ ማንም የለም (፪x)
ጌታዬ እንዳንተ ማንም የለም
እግዚአብሔር እንዳንተ ማንም የለም
ከአንተ በላይ ወዳጅ ማን አለ
ከአንተ በላይ ረዳት እኮ ማን አለ
ከአንተ በላይ ተስፋ ማን አለ
ከአንተ በላይ ረዳት እኮ ማን አለ
እግዚአብሔር እንዳንተ ማንም የለም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አምላኬ እንዳንተ ማንም የለም
እግዚአብሔር እንዳንተ ማንም የለም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ