ዋናዬ
Wanayie
ትራክ 8 · 5:58 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኢየሱስ የግል ነው የግል ነው
ኢየሱስ የግሌ ነው አየደል የጋራ
አልናጠቀውም ከማንም ጋራ
ኢየሱስ የግል ነው የግል ነው
ኢየሱስ የግልሌ ነው አየደል የጋራ
አልደራደርም ከማንም ጋራ
አዝማች · Chorus
ዋናዬ ኢየሱስ ነው ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው
ዋናዬን አላስነካም ካለ እሱ ትርፍም የለም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በኢየሱስ ከሚመጡብኝ የማገኘው ይቅርብኝ
በጌታ ከሚመጡብኝ የማገኘው ይቅርብኝ (፪x)
ጠላቴ ሊያጓጓኝ አንድ ነገር ቢያሳየኝ
ብኩርናዬን አልሽጥም የምስር ወጥ ይቅርብኝ
ከዔሳው ተምሬያለሁ ለምንም ሆኛለሁኝ
ጠላቴ ሊያጓጓኝ አንድ ነገር ቢያሳየኝ
ኢየሱስ አልሽጥም ሰላሳ ብር ይቅርብኝ
ከይሁዳ ተምርያለሁ ለምንም ሆኛለሁኝ
አዝማች · Chorus
ዋናዬ ኢየሱስ ነው ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው
ዋናዬን አላስነካም ካለ እሱ ትርፍም የለም
ቁጥር 3 · Verse 3
ዋናዬ ኢየሱስ ነው መኖር እንኳን ትርፍ ነው
ዋናዬን አላስነካም ካለ እሱ መኖር የለም
በኢየሱስ ከሚመጡብኝ የማገኘው ይቅርብኝ
በጌታ ከሚመጡብኝ የማገኘው ይቅርብኝ
በኢየሱስ ከሚመጡብኝ የሚሰጡኝ ይቅርብኝ
በጌታ ከሚመጡብኝ የሚሰጡኝ ይቅርብኝ
እሳቱ እጥፍ ቢነድም ለምስሉ አልሰግድም
እግዚአብሔር አምላኬ ነው አምኜው ነው ብሞትም
ሊገለጥ ካለው ክብር ሳስተያየው አይቆጭም
ለምን አንደመረጠኝ ይህንን አሰምራለሁ
ከሁሉም አስቀድሜ ጥሪዬን አከብራለሁ
የእምነት አባቶቼን ያለፉትን እያየሁ
እርሱን ለማክበር ለርሱ ለመኖር
እሽቀዳደማለሁ እሽቀዳደማለሁ (፫x)
እሽቀዳደማለሁ እሽቀዳደማለሁ
ከእንግዲህ እልደለል ለጊዜያዊ ነገር
እግዚአብሔር ያሰበልኝ የዘላለም ቁም ነገር
ከዚህ አይበልጥብኝም የቀረው ሁሉ ቢቀር
አወዳድሬ ይሻለኛል ብዬ እንዳልናገር
የእኔ ኢየሱስ ከምንም ጋር አይወዳደር
አስተያይቼ ይሻለኛል ብዬ እንዳልናገር
የእኔ እግዚአብሔር ከነጭራሹ አይወዳደር
ጭክን አድርጌ ቆርቻለሁ ለኢየሱስ ብቻ እኖራለሁ
አልመለስም ወደኋላ ጠላቴ መለከት ቢነፋ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ