አንተን ብቻ
Anten Becha
ትራክ 9 · 5:15 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ትኩር ብዬ ትክ ብዬ
አንተን ብቻ አያለሁ (፪x)
አይሃለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
እዛ ጋ አለው ዋጋ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ግራ ገብቶኝ ሲጨንቀኝ ሲጠበኝ
ኑሮ ትክት ሲለኝ አንተን ብቻ አያለሁ
መሄድ አቅቶኝ ስወድቅ ስነሳ
ጉልበቴም ሲላላ አንተን ብቻ አያለሁ
ዓይኖቼን ቀና አርጌ ያልከኝን አስታውሳለሁ
መከራዬንም ሃዘኔንም ያን ጊዜ እረሳዋለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
እዛ ጋ አለው ዋጋ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መድኃኒቴ የልቤ ወዳጅ
አንተ አትጥልምና አንተን ብቻ አያለሁ
አንዴ መለስ አንዴ ደግሞ ዞር
አያውቅህምና አንተን ብቻ አያለሁ
ደመና አይቼ አይደለም ጌታዬ ክበር የምልህ
በተስፋዬ ላይ ቆማለሁ በምድረ በዳ አይሃለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
እዛ ጋ አለው ዋጋ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ