መዳኔ
Medanie
ትራክ 4 · 5:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የትኛውም ላይ ልቤን አልጥልም
ጌታዬን ከማውቅ የቱም አይበልጥም
ሆነልኝ ከምለው በሕይወት ዘመኔ
አንዱና ትልቁ መዳኔ ነው ለእኔ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
መዳኔ መዳኔ
መዳኔ ነው ለእኔ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ምን ልይ ምን ልፍጠር ከዚህ በላይ
አዳነኝ እኮ ወርዶ ከላይ
በምህረቱ ደግሞ ሁሌ ልጄ ብሎ
አንዴ ወዶኛል ላይጠላኝ ምሎ (፪x)
አዝማች · Chorus
የትኛውም ላይ ልቤን አልጥልም
ጌታዬን ከማውቅ የቱም አይበልጥም
ሆነልኝ ከምለው በሕይወት ዘመኔ
አንዱና ትልቁ መዳኔ ነው ለእኔ (፪x)
መዳኔ መዳኔ
መዳኔ ነው ለእኔ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ለእኔ ስላረገው ያንሳል ምሥጋና
ከሞት አፋፍ ነው ያዳነኝና
ለእኔ ስላረገው ያንሰዋል አምልኮ
ከሲዖል ጣር ነው ያዳነኝ እኮ
ያንሳል አምልኮ ከሞት አፋፍ ነው ያዳነኝ እኮ
ያንሳል ምስጋና ከሲዖል ጣር ነው ያዳነኝና
አዝማች · Chorus
የትኛውም ላይ ልቤን አልጥልም
ጌታዬን ከማውቅ የቱም አይበልጥም
ሆነልኝ ከምለው በሕይወት ዘመኔ
አንዱና ትልቁ መዳኔ ነው ለእኔ (፪x)
መዳኔ መዳኔ
መዳኔ ነው ለእኔ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ