Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አመልክሃለሁ

Amelkehalehu

2014 · ትራክ 3 · 6:59 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አመልክሃለሁ ጌታ

እገዛልሃለሁ በደስታ (፪x)

ብዙ ምርኮን እንዳገኘ ሰው

እኔም በአንተ ደስ ተሰኘሁ (፪x)

እወድሃለሁ ብልህ መች ይገልፅልኛል

አፈቅርሃለሁ ብልህ መች ይገልፅልኛል

ምድራዊው ቃል ሁሉ እጅግ አንሶብኛል

ግን ደግነቱ አንተ መች ቃል ትቆጥራለህ

ይልቅ የውስጥ የልብን መመዝን ታዋቃለህ (፪x)

እንደ ወንዝ እንደ ጅረት

እንደሚጠጣ ገነት (፪x)

የፅድቅ ብዛት የአንተ ፀጋ

የተጠማችን ነፍስ የሚያረካ (፪x)

የሕይወትን ጥም የሚያረካ (፬x)

አመልክሃለሁ ጌታ

እገዛልሃለሁ በደስታ (፪x)

ብዙ ምርኮን እንዳገኘ ሰው

እኔም በአንተ ደስ ተሰኘሁ (፪x)

የምህረትህ ጥገኛ

የፍቅርህ ድግሞ እስረኛ (፪x)

ከአንተ ውጭ የለኝም ማንነት

ላፍሰው ልቤን በአንተ ፊት

ከአንተ ውጭ የለኝም ማንነት

ላፍሰው ልቤን በአንተ ፊት (፮x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ