ከፍ አድርጌ
Kef Adregie
2014 · ትራክ 8 · 5:28 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከፍ አድርጌ መለከቴን እነፋለሁ
ምሥጋናዬን አውጃለሁ (፪x)
ከፍጥረታት ጋር ተባብሬ
ያለ የሌለኝን ጭምሬ
እቀኛለሁ ለንጉሤ
ጌታ መጥቷል በመቅደሴ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
መድኃኒዓለም እውነትም አንተ እውነትም መድኃኒት ነህ
አባትህ ይህንን አውቆ ኢየሱስ ብሎህ ጠራህ
የባህሩ ምሳሌ የክብሩ ነፀብራቁ ነህ
የእኔንም ሕይወት ያደመቅህ የደስታዬ ፍፃሜው ነህ
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታዬ ዕድል ፈንታዬ
የዘላለም መኖሪያዬ
አምላክ የምለው አንተን ነው
ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ተቀበለው
ወዳጅ የምለው አንተን ነው
ምሥጋናዬን ተቀበለው (፪x)
ረዳት የምለው አንተን ነው
ምሥጋናዬን ተቀበለው
ቁጥር 3 · Verse 3
እያደር እያደር ዛሬማ እያደረ
ይገረመኝ ጀመረ የመዳኔ ነገር
እያደር እያደር ዛሬማ እያደረ
ይደንቀኝ ጀመረ የመዳኔ ነገር
ለካ ድኛለሁ ከሞት አምልጬ
የጠላቶችን እራስ ረግጬ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የሚያስደንቅ ነው መዳኔ
እንደበራለኝ ለእኔ
ኢየሱሴ ሆነልኝ
ማንም የማይወስድብኝ
መዳኔ ድንቅ ነው
መዳኔ ልዩ ነው (፫x)
አዝማች · Chorus
ከፍ አድርጌ መለከቴን እነፋለሁ
ምሥጋናዬን አውጃለሁ (፪x)
ከፍጥረታት ጋር ተባብሬ
ያለ የሌለኝን ጭምሬ
እቀኛለሁ ለንጉሤ
ጌታ መጥቷል በመቅደሴ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ