ዘንድሮማ
Zenderoma
2014 · ትራክ 12 · 7:32 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የማልጠብቀው በህልሜም በውኔ
የሠራዊት ጌታ እንዳሳየኝ በዓይኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኧረ ይሄማ ሌላ ነው ሌላ ሌላ ነው
ዘንድሮማ ሌላ ነው ሌላ ሌላ ነው
ኧረ ይሄማ ሌላ ነው ሌላ ሌላ ነው
መድኃኒቴ በሕይወቴ ለእኔ ያደረገው
ቁጥር 2 · Verse 2
መለኮታዊ ግርማ ሞገስ
ከአምላኬ ዙፋን ከላይ ሲፈስ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አየሁ ሕይወቴን ሲያረሰርስ (፪x)
አየሁ ኑሮዬን ሲያረሰርስ (፪x)
የናፈኳቸው የሞተስ ምንጮጭ
ተከፍተውልኝ የሰማይ ደጆች
አየሁ ሲያጠግቡኝ የእግዚአብሔር እጆች (፪x)
አየሁ ሲያጠግቡኝ የእግዚአብሔር እጆች (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የማልጠብቀው በህልሜም በውኔ
የሠራዊት ጌታ እንዳሳየኝ በዓይኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኧረ ይሄማ ሌላ ነው ሌላ ሌላ ነው
ዘንድሮማ ሌላ ነው ሌላ ሌላ ነው
ኧረ ይሄማ ሌላ ነው ሌላ ሌላ ነው
መድኃኒቴ በሕይወቴ ለእኔ ያደረገው
ቁጥር 5 · Verse 5
የትንቢቱ ቃል ሥጋን ለበሰ
የተወሰደው ምርኮ ተመለሰ (፪x)
ይኸው እንደ ንሥር ኃይሌ ታደሰ (፪x)
ይኸው እንደ ንሥር ኃይሌ ታደሰ (፪x)
የልምላሜ የመጐገብኘት
የሞገስና የመፅናናት
አንድ ነው ምንጩ የበረከት (፪x)
አንድ ነው ምንጩ የበረከት (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ፍቅርህ ይጣፍጣል (፫x)
ማራ የሆነውን መራራውን
ሕይወት ያጣፍጣል
ይጣፍጣል ይጣፍጣል
ፍቅርህ ይጣፍጣል (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ደስ ያለው ሰው በአምላኩ የኮራ
ምን ያደርጋል እስኪ ንገሩኛ
ደስ ያለው ሰው በኢየሱስ የኮራ
ምን ያደርጋል እስኪ ንገሩኛ
ማመልክ ነው እንጂ
ይህንን ድንቅ ጌታ (፬x)
ደስ ያለው ሰው በኢየሱስ የኮራ
ምን ያደርጋል እስኪ ንገሩኛ
ማመልክ ነው እንጂ
ይህንን ድንቅ ጌታ (፬x)
ቁጥር 8 · Verse 8
የማይገርም ካለ የእግዚአብሔርን ጥበብን አይቶ
አሃሃሃ አይቶ
ይህ ህመም ነው እንጂ አይደለም ጤንነት ከቶ
አሃሃሃ ከቶ
አሥር ጊዜ አይኖር የሚኖረው አንዴ
አሃሃሃ አንዴ
ሰው ለእግዚአብሔር ኖሮ ቢሞትስ ይቆጨዋል እንዴ
አሃሃሃ እንዴ
አሥር ጊዜ አይኖር የሚኖረው አንዴ
አሃሃሃ አንዴ
ለኢየሱሴ ኖሬ ብሞትስ ይቆጨኛል እንዴ
አሃሃሃ እንዴ (፪x)
ቁጥር 9 · Verse 9
ለውዴ አሃሃሃ ለውዴ (፪x)
ለውዴ ኦሆሆሆ ለውዴ
ለውዴ አሃሃሃ ለውዴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ