የቀደስካቸው
Yeqedeskachew
2014 · ትራክ 9 · 5:26 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የቀደስካቸው እጆቼን አንስቼ
ማምለክ ስጀምር ዓይኖቼን ወደላይ አቅንቼ (፪x)
ህዋሳቶቼ አካላቶቼ
አንተን ይሉኛል አጥንቶቼ
ህዋሳቶቼ አካላቶቼ
አንተን ይሉኛል አጥንቶቼ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለሰው ልጅ ልማድነቱ
ክብርና ሞገስ በሕይወቱ
ለስብዕናውም ትርጉም
ከአንተ ውጭ አልተገኘም
ከአንተ ሌላ የለም የለም
አማራጭ የሌለህ ምርጫዬ
የሕይወቴ ገነት ተድላዬ
ያለ አንዳች ቅንጣት ቅሬታ
ፈቅጄ የማመልክህ በደስታ
እድል ፈንታዬ የእኔ ጌታ
አዝማች · Chorus
የቀደስካቸው እጆቼን አንስቼ
ማምለክ ስጀምር ዓይኖቼን ወደላይ አቅንቼ (፪x)
ህዋሳቶቼ አካላቶቼ
አንተን ይሉኛል አጥንቶቼ
ህዋሳቶቼ አካላቶቼ
አንተን ይሉኛል አጥንቶቼ
ቁጥር 2 · Verse 2
አጥንት ከአጥንት ሳይዋደድ
ሳልሰራ በእናቴ ሆድ
ቀኖቼን ጽፈህ በመጽሐፍ
እንደ ፈቃድህ እንደ ሀሳብህ
አራመድከኝ በትንቢት ቃልህ
አጋጣሚ አይደል ዎይ በድንገት
የሆንኩትን ሁሉ የሆንኩት
የሕይወቴን አቅጣጫ ቀያሪ
ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ
አንተ ነህ የልቤ መርማሬ
አዝማች · Chorus
የቀደስካቸው እጆቼን አንስቼ
ማምለክ ስጀምር ዓይኖቼን ወደላይ አቅንቼ (፪x)
ህዋሳቶቼ አካላቶቼ
አንተን ይሉኛል አጥንቶቼ
ህዋሳቶቼ አካላቶቼ
አንተን ይሉኛል አጥንቶቼ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ