Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የናርዶስ ሽቶዬ

Yenardos Shetoyie

2014 · ትራክ 4 · 6:19 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የናርዶስ ሽቶዬ የአልባስጥሮስ

መጓደጃዬ ውድ ኢየሱስ

ልቤ ከልብህ ጋር ተቆራኝቶ

መኖር ወደደ አንተን አግኝቶ (፪x)

አንተን አግኝቶ (፬x)

ቅዱሱ እግዚአብሔር የማውቀህ ከልጅነቴ

ንጉሡ እግዚአብሔር የምሻህ ከልጅነቴ

እርስቴም ተድላዬም ጥጋቤም

አንተ ነህ ማር እና ወተቴ (፭x)

የቆላ አበባ ፅጌረዳዬ

የእግዚአብሔር ልጅ ውሎ መግቢያዬ

በማሰማሪያህ በታዛ ሥር

አንተን ሳመልክህ ውዬ ልደር (፭x)

ውዬ ልደር (፬x)

መጣሁኝ ወዳሳየኸኝ ውብ ሥፍራ

አየሁ የግርማህን ፀዳል ሲያበራ

ወዳጄ ለመሆኑ ሰው አወቀህ ወይ

ቁንጅናህ ለሀገር የሚተርፍ አይደል ወይ (፫x)

ቅዱሱ እግዚአብሔር የማውቀህ ከልጅነቴ

ንጉሡ እግዚአብሔር የምሻህ ከልጅነቴ

እርስቴም ተድላዬም ጥጋቤም

አንተ ነህ ማር እና ወተቴ (፭x)

ልቤ መልካምን ቅኔ አፈለቀ

ንጉሡን ጌታ እያደነቀ

ውበቱ ከአምራል ከሰው ይልቅ

የእኔማ ኢየሱስ ከብርቅም ብርቅ (፬x)

ቅዱሱ እግዚአብሔር የማውቀህ ከልጅነቴ

ንጉሡ እግዚአብሔር የምሻህ ከልጅነቴ

እርስቴም ተድላዬም ጥጋቤም

አንተ ነህ ማር እና ወተቴ (፱x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ