መነሻህ ከፍታ
Meneshah Kefeta
2014 · ትራክ 2 · 6:58 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከሰማሁትና ይበልጣል
ልዑል ሆይ መዓዛህ ያውዳል
ከመንግስትህ ህግ ሁኔታ
መች ተነገረ ለአንተ ጌታ (፪x)
ከጥበብህ ህግ ሁኔታ
መች ተዘመረ ለአንተ ጌታ
መች ተዘመረ ለአንተ ጌታ (፪x)
አዝማች · Chorus
መነሻህ ከፍታ መድረሻህ ከፍታማ
ጅማሬህ ከፍታ ፍፃሜህ ከፍታማ
ዙፋንህን ዘርግትህ ከፍ ባለው ቦታ
ፀንተህ ትኖራለህ የእኔ ጌታ (፪x)
ፀንተህ ትኖራለህ የእኔ ጌታ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የምድር ጠቢባን ሊቃውንቱ
የፍጥረትን ጥያቄ መች ፈቱ
የጥበብ የእውቀት የሥልጣኔ
መጀመሪያው አንተው ነህ መድህኔ
መጨረሻው አንተው ነህ መድህኔ (፪x)
ሊቃውንቱ እንዲህ ይበሉ
ኃያላኑ እንዲህ ይበሉ
ጠቢባኑ እንዲህ ይበሉ
ሠራዊቱ እንዲህ ይበሉ
ኤልሻዳይ እግዚአብሔር ብቻ
ሁሉን ቻይ እግዚያብሔር ብቻ
ኤሎሂም እግዚአብሔር ብቻ
አዶናይ እግዚአብሔር ብቻ (፪x)
እግዚአብሔር ብቻ (፰x)
ከምድር ዳርቻ እስከ ጫፍ
ከሠማይም አፅናፍ እስከ አፅናፍ
ከትውልድ የትውልዶች መካከል
መች ተገኘ አንተን የሚስተካከል
መች ተገኘ አንተን የሚስተካከል (፪x)
አዝማች · Chorus
መነሻህ ከፍታ መድረሻህ ከፍታማ
ጅማሬህ ከፍታ ፍፃሜህ ከፍታማ
ዙፋንህን ዘርግትህ ከፍ ባለው ቦታ
ፀንተህ ትኖራለህ የእኔ ጌታ (፪x)
ፀንተህ ትኖራለህ የእኔ ጌታ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከፍ ከፍ (፪x) ብለህ
ከፍ ከፍ ብለህ
የክብር የምሥጋናን ዘውድ ተጭነህ
በማይናወጠው ፅኑ መንግስትህ
ያለ ተቀናቃኝ ትገዛናለህ (፪x)
ኤልሻዳይ እግዚአብሔር ብቻ
ሁሉን ቻይ እግዚያብሔር ብቻ
ኤሎሂም እግዚአብሔር ብቻ
አዶናይ እግዚአብሔር ብቻ (፪x)
እግዚአብሔር ብቻ (፲፮x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ