Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንተ የልቤ ወዳጅ ነህ

Ante Yelebie Wedaj Neh

2014 · ትራክ 6 · 6:43 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንተ የልቤ ወዳጅ

አንተ የነፍሴ ወዳጅ

የት ታሰማራለህ ንገረኝ

ልምጣ ላገልገል ከአንተ ደጅ

የት ታሰማራለህ ንገረኝ

ልምጣ ላገልገል ከአንተ ደጅ (፪x)

አንደበቴን መክፈት ስጀምር

ውልታህን ስደረድር (፪x)

የአምላክ መንፈስ መጣ በላዬ

ተገናኘኝ በጓዳዬ (፪x)

አይጠገብ ታይቶ ታይቶ

እንደ እርሱ የት ተገኝቶ (፪x)

በየማለ ተው አዲሰ ሙሽራዬ ኢየሱስ

በየማለ ተው አዲሰ እንግዳዬ ኢየሱስ

አንተ የልቤ ወዳጅ

እኮ አንተ የነፍሴ ወዳጅ

የት ታሰማራለህ ንገረኝ

ልምጣ ላገልገል ከአንተ ደጅ (፪x)

ከፍታና ወርዱ ጥልቀቱ

አይገመት ስፋት ርዝመቱ (፪x)

ደጉ ኢየሱስ የዋህ ትሁቱ

ምን ዓይነት ነው የፍቅር ብርቱ (፪x)

አይጠገብ ታይቶ ታይቶ

እንደ እርሱ የት ተገኝቶ (፪x)

በየማለ ተው አዲሰ ሙሽራዬ ኢየሱስ

በየማለ ተው አዲሰ እንግዳዬ ኢየሱስ (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ