Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍፁም እንከን የለው ውበትህ

Fetsum Enken Yelew Webeteh

2014 · ትራክ 5 · 5:43 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እኔማ ቢሆንልኝማ

በክብርህ ውስጥ አድሬ

በህልውናህ ኖሬ

ያን መልካሙን ፈትህን

ታይቶ የማይጠገበውን

ካገኘሁ ያኔ ኖርኩኝ/ረካሁ እላለሁ (፪x)

ፍፁም እንከን የሌው ውብትህ

ደናግሎች አይተው ወደድዱህ (፪x)

ሳበኝ እሮጣለሁ ከኋልህ

ሳይህ ውዬ ባድር አልጠግብህ

ሳይህ ውዬ ባድር አልጠግብህ (፪x)

አልጠግብህ (፮x)

አልጠግብህ ጌታ አልጠግብህ

የዕድሜ ልክ ፍስሃ በቀኝህ

የሚያበራ ፀዳል ስላለህ (፪x)

ፃድቅ በብርሃንህ ይራመዳል

ከህልውናህ ውጭ የት ይኬዳል (፪x)

እኔማ ቢሆንልኝማ

በክብርህ ውስጥ አድሬ

በህልውናህ ኖሬ

ያን መልካሙን ፈትህን

ታይቶ የማይጠገበውን

ካገኘሁ ያኔ ኖርኩኝ/ረካሁ እላለሁ (፪x)

የተትረፈረፈ ነው ፅዋዬ

ከአምላክ ፊት ሆኖልኝ ገበታዬ (፪x)

የንጉሥ ማዕረግ ለምዳለች ነፍሴ

ተጣብቃልኝ በኢየሱሴ (፪x)

በኢየሱሴ (፰x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ