የዘውትር
Yezewter
2014 · ትራክ 11 · 6:05 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የፍቅሬ መሃል ነህ የመወደዴም ቅኔ
አንዳች አልቆጥብም አሰማለሁ እኔ
የመስዋዕቴን በኩራት የፍቅሬን ፍታ
አዘጋጅቻለሁ ላፈሰው ለጌታ (፪x)
አዝማች · Chorus
ለእኔስ የዘውትር ጥማቴ
መሻት የቀን የሌሊት ናፍቆቴ
የአንተን ክብር ማየቴ
በዕድሜ በሰጠኸኝ ዘመኔ
ቁጥር 2 · Verse 2
በዕድሜ በሰጠኸኝ ዘመኔ (፪x)
የወርቅ ፍልቃቂ የክብር ሙዳዬ
በሞገስ ያጌጥከው መጐናፀፊያዬ
የፊቴ መድኃኒት የርስቴ ዕድል ፈንታ
ከአንተ ሌላ አላውቅም የልጅ ልጅ ደስታ (፪x)
አዝማች · Chorus
ለእኔስ የዘውትር ጥማቴ
መሻት የቀን የሌሊት ናፍቆቴ
የአንተን ክብር ማየቴ
በዕድሜ በሰጠኸኝ ዘመኔ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከደስታዬ በላይ አንተን ወድጃለሁ
ፅድቅን መከታተል ተለማምጃለሁ
ሌላ ሌላውማ መች ልቤ ደረሰ
የአንተ ዘይት ብቻ ሕይወቴን አራሰ
ሌላ ሌላውማ መች ልቤ ደረሰ
የአንተ ቅባት ብቻ አንጀቴን አራሰ
አዝማች · Chorus
ለእኔስ የዘውትር ጥማቴ
መሻት የቀን የሌሊት ናፍቆቴ
የአንተን ክብር ማየቴ
በዕድሜ በሰጠኸኝ ዘመኔ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ