Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አመሰግናለሁ

Amesegenalehu

ትራክ 10 · 5:31 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አመሰግናለሁ አመሰግናለሁኝ አመሰግናለሁ (፪x)

ፍቅሩ ልቤን ተናገረው

እንዲያመልከው አነሳሳው

ሥራው ልቤን ተናገረው

እንዲያመልከው አነሳሳው

አመሰግናለሁ አመሰግናለሁኝ አመሰግናለሁ (፪x)

ዘወትር ማለዳ ቀንና ሌሊቱ

እያልኩኝ አልፋለሁ አቤት ምህረቱ

ከመቅደሱ ሆኖ እርሱም ይሰማኛል

እኔስ ምሥጋናዬ በእርሱ ዘንድ ተወዷል

ፍቅሩ ልቤን ተናገረው

እንዲያመልከው አነሳሳው

ሥራው ልቤን ተናገረው

እንዲያመልከው አነሳሳው

አመሰግናለሁ አመሰግናለሁኝ አመሰግናለሁ (፪x)

ቃላቶች ሳይወጡ የሚጐተጉቱ

አመስግነኝ ብሎ ጌታስ በአንደበቱ

ስራ እና ፍቅሩ መች ያስቀምጠኛል

ልቤስ በፈቃዱ ላመስግነው ብሏል

ፍቅሩ ልቤን ተናገረው

እንዲያመልከው አነሳሳው

ሥራው ልቤን ተናገረው

እንዲያመልከው አነሳሳው

አመሰግናለሁ አመሰግናለሁኝ አመሰግናለሁ (፪x)

ልቤ አሰበ ፍቅሩን

እጅግ መወደዱን

ተነሳ ለአምልኮ

ጌታውን ፈልጐ (፪x)

ነፍሴ ታዳጊዋን ታመሰግናለች

ከአዳኞች ወጥመድ ድኛለው ትላለች

በፀናችው ክንዱ እግዚአብሔር ታድጐ

የራሱ አድርጐኛል ምሥጋናን ፈልጐ

ፍቅሩ ልቤን ተናገረው

እንዲያመልከው አነሳሳው

ሥራው ልቤን ተናገረው

እንዲያመልከው አነሳሳው

አመሰግናለሁ አመሰግናለሁኝ አመሰግናለሁ (፪x)

ልቤ አሰበ ፍቅሩን

እጅግ መወደዱን

ተነሳ ለአምልኮ

ጌታውን ፈልጐ (፪x)

አመሰግናለሁ አመሰግናለሁኝ አመሰግናለሁ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ