ጌታን እወደዋለሁ
Gietan Ewedewalehu
ትራክ 8 · 5:30 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሰራኸውን ሳስተውለው ዞሬ
አልጨርሰውም ሁሉንም ዘርዝሬ
በፍቅር ቃላት እኔ ይህንን እላለሁ
የወደደኝን እኔም እወደዋለሁ
ጌታን እወደዋለሁ (፬x)
አዝማች · Chorus
አንደበቴን ቀብቶታል
ጌታ ኑሮዬን ባርኮታል (፪x)
ታዲያ ምኑ ዝም ያሰኘኝ
ሁሌ ክብሩን እያሳየኝ (፪x)
ክበር ልበል ክበር እንጂ
ንገሥ ልበል ንገሥ እንጂ
ሌላ ቃላት ስለሌለኝ
ሾሜሃለው ንገስልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ማነው የገመተ እዚህ ይደርሳል በሎ
ጠላት ያለውን ወሬ ተቀብሎ
ጌታ ሰው አረገኝ ጠላቴም አፈረ
ማቄንም ቀደደ ቀንበሬን ሰበረ
ጌታ ሰው አድርጐኛል (፬x)
አዝማች · Chorus
አንደበቴን ቀብቶታል
ጌታ ኑሮዬን ባርኮታል (፪x)
ታዲያ ምኑ ዝም ያሰኘኝ
ሁሌ ክብሩን እያሳየኝ (፪x)
ክበር ልበል ክበር እንጂ
ንገሥ ልበል ንገሥ እንጂ
ሌላ ቃላት ስለሌለኝ
ሾሜሃለው ንገስልኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ባረከው ሕይወቴን ባረከው ኑሮዬን
ስሾመው በላዬ ሳመልከው ጌታዬን
በቀሪው ዘመኔም ጌታ ይንገስበት
በሰጠኝም ሕይወት እርሱ ይሰልጥንበት
ጌታን እሾመዋለሁ (፪x)
ጌታን አነግሰዋለሁ(፪x)
አዝማች · Chorus
አንደበቴን ቀብቶታል
ጌታ ኑሮዬን ባርኮታል (፪x)
ታዲያ ምኑ ዝም ያሰኘኝ
ሁሌ ክብሩን እያሳየኝ (፪x)
ክበር ልበል ክበር እንጂ
ንገሥ ልበል ንገሥ እንጂ
ሌላ ቃላት ስለሌለኝ
ሾሜሃለው ንገስልኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ