ጌታ እርሱ ብቻ ነው
Gieta Esu Becha New
ትራክ 9 · 5:28 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በላይ በላይ በላይ በሰማይ
በታች በታች ሆነህ በምድር ላይ (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ እርሱ ብቻ ነው (፪x)
ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው
አምላክ እርሱ ብቻ ነው (፪x)
ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው
ቁጥር 2 · Verse 2
ዛሬስ የታሉ ታላቅ ነን ያሉ
ዓመታት ሲያልፉ አብረው አለፉ
የሁሉ ገዢ የሁሉ የበላይ
የእኛ አምላክ ግን አለ በሰማይ (፭x)
አዝማች · Chorus
ጌታ እርሱ ብቻ ነው (፪x)
ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው
አምላክ እርሱ ብቻ ነው (፪x)
ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው
ቁጥር 3 · Verse 3
አላየሁኝም የሚመለክ እንደ እርሱ
አላየሁኝም የሚወደድ እንደ እርሱ
አልሰማሁኝም የሚመለክ እንደ እርሱ
አልሰማሁኝም የሚወደድ እንደ እርሱ
የምትወዱት ከእኔ ጋራ ተነሱ
የሚገባውን ክብር እንስጥ ለእርሱ (፪x)
በላይ በላይ በላይ በሰማይ
በታች በታች ሆነህ በምድር ላይ (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ እርሱ ብቻ ነው (፪x)
ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው
አምላክ እርሱ ብቻ ነው (፪x)
ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው
ቁጥር 4 · Verse 4
የአህዛብ አማልክት የሚያመልኳቸው
የማይሰሙና ማያዩ ናቸው
ሰምቶ በእሳት የሚመልሰው
የምናመልከው እግዚአብሔር ብቻ ነው (፬x)
አዝማች · Chorus
ጌታ እርሱ ብቻ ነው (፪x)
ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው
አምላክ እርሱ ብቻ ነው (፪x)
ፍጥረት ወዶ ሚያመልከው
ቁጥር 5 · Verse 5
ያለውና የነበረው የሚመጣው
ሁሌ ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ ነው
አልፋ እና ኦሜጋ እኔ ነኝ ብሏል
ወዶ ፈቅዶ ፍጥረትም ያመልከዋል (፪x)
ጌታ እርሱ ብቻ
አምላክ እርሱ ብቻ
ገዢ እርሱ ብቻ
ንጉሥ እርሱ ብቻ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ