Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ለእኔ የምታስበው

Lenie Yemetasebew

ትራክ 4 · 6:43 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለእኔ የምታስበው ይበልጣል

ለሰው የማይቻል ለአንተ ይቻላል

እኔ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ

መታመኔን በአንተ አደርገዋለሁ

ጌታን እጠብቃለሁ አንተን እጠብቃለሁ (፪x)

የሳቁ ነበሩ በአንተ ስታመን

ትፈታዋለህ ስል እንቆቅልሼን

ጠላቴም ወዳጄም ስታስበኝ አዩ

የሚያመልከው አምላክ ለካ ይሰማል አሉ (፪x)

ለእኔ የምታስበው ይበልጣል

ለሰው የማይቻል ለአንተ ይቻላል

እኔ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ

መታመኔን በአንተ አደርገዋለሁ

ጌታን እጠብቃለሁ አንተን እጠብቃለሁ (፪x)

ቃልህን አምናለሁ አይደለም ስሜቴን

እንደምትሞላው መሻቴን የውስጤን

ፍፃሜና ተስፋ የምትሰጠዉ

ሃሳብህ ይበልጣል እጠብቃለሁ (፪x)

ለእኔ የምታስበው ይበልጣል

ለሰው የማይቻል ለአንተ ይቻላል

እኔ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ

መታመኔን በአንተ አደርገዋለሁ

ጌታን እጠብቃለሁ አንተን እጠብቃለሁ (፪x)

በአንተ እታመናለሁ አልነዋወጥም

ወደ ግራና ቀኝ አማራጭ አላይም

ግድ ይልሃልና ጌታ የእኔ ነገር

ከአንተ እጠብቃለሁ ወደሌላው ሳልዞር (፪x)

አንተን ብቻ እጠብቃለሁ

ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ

የሕይወት ቃል አለህና

ለዘላለም የሚያጸና (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ