በችኮላ ከቶ አልወጣም
Bechekola Keto Alwetam
ትራክ 5 · 3:16 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በማስተዋል አደርጋለሁ
እረኛዬን እሰማዋለሁ
ያውቃል ከእኔ በብዙ ሺህ
ነፍሴ ይምራሽ አምላክሺ
ቀድሞ አይቶ የእኔን መንገድ
መራኝ በድንቅ በእርሱ ፈቃድ
ግራ ቀኜን ስላየልኝ
ተማምኜ እወጣለሁኝ
አዝማች · Chorus
በችኮላ ከቶ አልወጣም
በመኮብለል ደግሞ አልሄድም
እግዚአብሔር ይቀድመኛል
በፈቃዱ ይመራኛል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በድንኳኔ እጠብቃለሁ
የአንተን ትእዛዝ እሰማለሁ
ውጣ ካልከኝ እወጣለሁ
ጠላቶቼን እመታለሁ
ጠላት ለእኔ ለሚያስበው
ግድም አይለኝ ስለሚለው
የእግዚአብሔር ኃይል ሸፍኖኛል
ደሙ እርሱ እኔን ስቦኛል
አዝማች · Chorus
በችኮላ ከቶ አልወጣም
በመኮብለል ደግሞ አልሄድም
እግዚአብሔር ይቀድመኛል
በፈቃዱ ይመራኛል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ