በዘመኔ ሁሉ
Bezemenie Hulu
ትራክ 12 · 3:56 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
“ሃሌሉያ ሃሌሉያ”
ሁልጊዜ እግዚአብሔርን እባርከዋለሁ
ምሥጋናው ዘወትር ዘወትር በአፌ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አቤቱ በኃይልህ ጌታ በችሎትህ
እዚህ ደርሻለው እስቲ ላመስግንህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ነው
ምሥጋና ምሥጋና ነው ያለው
ዝማሬ ዝማሬ ነው
ዝማሬ ዝማሬ ነው ያለው
ቁጥር 3 · Verse 3
በዘመኔ ሁሉ ላረክልኝ ነገር
ተመሥገን ሌላ እኔ ምን ልናገር (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ነው
ምሥጋና ምሥጋና ነው ያለው
ዝማሬ ዝማሬ ነው
ዝማሬ ዝማሬ ነው ያለው
ቁጥር 4 · Verse 4
ትዝታዬ እኮ ነህ በቀን በሌሊት
ቃሌም ንግግሬም ኢየሱስ ሆንክበት
ትዝታዬ እኮ ነህ በቀን በሌሊት
ቃሌም ንግግሬም ምሥጋና አለበት
ቁጥር 5 · Verse 5
አቤቱ በኃይልህ ጌታ በችሎትህ
እዚህ ደርሻለው እስቲ ላመስግንህ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ይህች ቀን ናትና አንተ የሰራሃት
በሷ ደስ ይለኛል አደርጋለው ሀሴት (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
አቤቱ በኃይልህ ጌታ በችሎትህ
እዚህ ደርሻለው እስቲ ላመስግንህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ነው
ምሥጋና ምሥጋና ነው ያለው
ዝማሬ ዝማሬ ነው
ዝማሬ ዝማሬ ነው ያለው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ