ጠላት ተመቷል
Telat Temetual
ትራክ 6 · 5:24 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እባብና ጊንጡን አስረግጦናል
በጠላት ኃይልም ላይ ሥልጣን ሰጥቶናል
የሰላም አምላክ እግራችን ሥር ቀጥቅጦታል
የሚያስቆመንም የለም ጠላት ተመቷል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የጌታን ዕቃ ጦር እንለብሳለን
አይደል በደም ሥጋ መጋደላችን
የዲያቢሎስን ሽንገላ ተቃውመን
በአለቆች ስልጣናት ላይ እንዘምታለን
የሚንበለበለውን የክፉ ፍላፃ
እናጠፋዋለን አለን የእምነት ጋሻ
አዝማች · Chorus
እባብና ጊንጡን አስረግጦናል
በጠላት ኃይልም ላይ ሥልጣን ሰጥቶናል
የሰላም አምላክ እግራችን ሥር ቀጥቅጦታል
የሚያስቆመንም የለም ጠላት ተመቷል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እርሱ ከኛ ጋር ነው ማን ይቃወመናል
በሕይወት ጐዳና ይኸው አራምዶናል
እጃችንን ይዞ መቼ ማድረስ ብቻ
በድል አሻግሮናል የሞትን ዳርቻ
እርሱ ኃይላችን ነው መመኪያ ክብራችን
መቼም አንወድቅም አለ ከጐናችን
አዝማች · Chorus
እባብና ጊንጡን አስረግጦናል
በጠላት ኃይልም ላይ ሥልጣን ሰጥቶናል
የሰላም አምላክ እግራችን ሥር ቀጥቅጦታል
የሚያስቆመንም የለም ጠላት ተመቷል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በኃይል አይደለም በብርታት
የጠላት እንዲህ መመታት
በመንፈስ እንጂ በእግዚአብሔር
ክንዱን ተማምኖ በሚኖር (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ