አምጡ
Amtu
ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ገና አለኝ ምሥጋና (፬x)
ገና ገና መቼ ይበቃውና (፪x)
ገና ገና ዛሬም እንደገና (፪x)
ገና ገና እሰዋለሁ ገና (፪x)
ገና አለኝ ምሥጋና (፬x)
አልጠግብም ባመሰግነው ተመስገን ተመስገን ብለው
ኢየሱስ ለእኔ ያረገው ውለታው እጅግ ብዙ ነው
አልውልም ሳላነሳሳው ሥሙ እንደሚፈስ ዘይት ነው
እንደገና አከብረዋለሁ ምሥጋናዬ እስኪ ይድረሰው
አዝማች · Chorus
አምጡ ምሥጋና አምጡ (፬x)
አምጡ ዝማሬ አምጡ (፬x)
አምጡ ዕልልታ አምጡ (፬x)
አምጡ ጭብጨባ አምጡ (፬x)
ጨምሩ ለጌታ ጨምሩ (፬x)
በተዋበ ዜማ ዘምሩ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሀያ አራት ሽማግሌዎች ወድቀው ክብርን ይሰጡሀል
መላዕክት ቅዱስ ቅዱስ ይገባሀል ለአንተ ይሉሀል
እኔም ባለችኝ ጊዜዬ ላክብርህ ውዱ ጌታዬ
ምሥጋና ምሥጋና እላለሁ ጌታ ነህ ባለውለታዬ
ገና አለኝ ምሥጋና (፬x)
ገና ገና መቼ ይበቃውና (፪x)
ገና ገና ዛሬም እንደገና (፪x)
ገና ገና እሰዋለሁ ገና (፪x)
አዝማች · Chorus
አምጡ ምሥጋና አምጡ (፬x)
አምጡ ዝማሬ አምጡ (፬x)
አምጡ ዕልልታ አምጡ (፬x)
አምጡ ጭብጨባ አምጡ (፬x)
ጨምሩ ለጌታ ጨምሩ (፬x)
በተዋበ ዜማ ዘምሩ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ